Arbaminch General Hospital

Arbaminch General Hospital ይህ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ትክክለኛው የፌስቡክ ገጽ ነው!

ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት የመደበኛ ክትባትን ተደራሽነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል __________የዓለም ፖሊዮ ቀን "አንድ ቀን፣ አንድ ትኩረት፣ የልጅነት ልምሻን/ፖሊዮን ጨርሶ ማጥፋት!" በሚል መ...
26/10/2026

ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት የመደበኛ ክትባትን ተደራሽነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል
__________

የዓለም ፖሊዮ ቀን "አንድ ቀን፣ አንድ ትኩረት፣ የልጅነት ልምሻን/ፖሊዮን ጨርሶ ማጥፋት!" በሚል መሪ መልዕክት በመናገሻ ቼሻየር ኢትዮጵያ ተከብሯል።

መንግስት ፖሊዮን ለማጥፋት በወሰደው ቁርጠኛ እርምጃ በርካታ ህፃናትን ከህመምና ከአካል ጉዳት መከላከል እንደተቻለ የጠቆሙት በጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ ፕሮፌሰር ስለሺ ጋሮማ ምንም እንኳ የመደበኛ ክትባት ተደራሽነት ከ90 በመቶ በላይ ቢሆንም ፖሊዮን ጨርሶ ለማጥፋት ተደራሽነቱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዓለም ፖሊዮ ቀን መሪ መልዕክት ፖሊዮን ለማጥፋት ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል ያሉት የዓለም ጤና ድርጅትንና አጋር ድርጅቶችን በመወከል መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር ቢጆይ ፒ ናምቢየር በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከሀገር ከዋይልድ ፖሊዮ ነፃ ብትሆንም በድንበር አካባቢ ከአጎራባች ሀገራት በሚመጣ የፖሊዮ ቫይረስ የተያዙ ህፃናት መገኘታቸውን በመጠቆም ቀሪ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

የገፈርሳ ጉጅ ክፍለ ከተማ ሃላፊ አቶ ረጋሳ ታደሰም የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ክትባት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ቼሻየር ኢትዮጵያ ለክትባት አገልግሎት ለክፍለ ከተማው ለሚያደርገው ድጋፍ አመስግነዋል።

ቼሻየር ኢትዮጵያ በ1954 ዓ ም እንደተቋቋመና በተለያዩ ምክንያቶች የአካል ጉዳት ላጋጠማቸው ህፃናትና አዋቂዎች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የገለፁት ደግሞ የቼሻየር ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፋሲል አየለ ናቸው።

በዕለቱ የዓለም ጤና ድርጅት ለቼሻየር ኢትዮጵያ የዊልቸር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የተጠቃሚ ምስክርነትና የፓናል ውይይትም በመድረኩ ተካሂዷል።

የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የመስከረም ወር አፈፃፀም እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ውይይት አካሄደ።                           ጥቅምት 13/2019 ዓምየአ...
23/10/2026

የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የመስከረም ወር አፈፃፀም እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ ውይይት አካሄደ።
ጥቅምት 13/2019 ዓም

የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል የመስከረም ወር አፈፃፀም Performance Monitoring Team(PMT) እና አጠቃላይ የአገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ እና የየክፍሉ ተዋካዮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት ጠለቅ ያለ የጋራ የውይይት መድረክ አካሂዷል ከዚህ ጋር ተያይዞ የመስከረም ወር አፈፃፀም በልማት ዕቅድ ባለሙያ በሆኑት በአቶ ቁምላቸው ከበደ ቀርቧል።

መድረኩን የመሩት የሆስፒታሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ አጠቃላይ ሪፖርቱን በተመለከተ መልካም ውጤቶችን እንዲቀጥሉ በማሳሰብ መሻሻል በሚገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጠለቅ ያለ ሀሳብ በማስተላለፍ በቀጣይነት መሻሻል የሚገባቸው ነገሮች እንዲሻሻሉ ከተጠያቂነት ኃላፊነት እንደተሰጣቸውም ለእያንዳንዱ የሥራ ክፍል አስተላልፈዋል።

በተጨማሪም የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አዲሱ አክለውም ምንም አይነት ከሕክምና አገልግሎት ጉድለት እና መስተጓጎል ጋር የሚያያዙ ጉዳዮች ቀይ መስመር መሆኑን በማሳሰብ እያንዳንዱ ባለሙያ ለተሻለ አገልግሎት መትጋት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩም የተለያዩ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በእያንዳንዱ የአገልግሎት ክፍል ውስጥ የታዩ ክፍተቶች መሻሻል እንደሚገባቸው በመተማመን ውይይቱን በተሳካ ሁኔታ አጠናቀዋል።


!!

Interim Guidelines for Ebola Disease Specimen Collection Managementhttps://ephi.gov.et/wp-content/uploads/2026/10/Interi...
22/10/2026

Interim Guidelines for Ebola Disease Specimen Collection Management
https://ephi.gov.et/wp-content/uploads/2026/10/Interim_Guidelines_for_Ebola_Disease_Specimen_Collection_Management-3.pdf

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድን በጋሞ ዞን ባደረገው ምልከታ ላይ ግብረ መልስ ሰጠ‎​አርባ ምንጭ፡-ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም(የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)‎​የደቡ...
22/10/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድን በጋሞ ዞን ባደረገው ምልከታ ላይ ግብረ መልስ ሰጠ

‎​አርባ ምንጭ፡-ጥቅምት 12/2019 ዓ.ም(የጋሞ ዞን ጤና መምሪያ)

‎​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤናው ሴክተር የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትል ቡድን በጋሞ ዞን ዳራማሎ እና ገረሴ ዙሪያ ወረዳዎች በሚገኙ የጤና ተቋማትና የኅብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ያደረገውን ድጋፋዊ ክትትል በማጠናቀቅ፣ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ግብረ መልስ ሰጥቷል።

‎​ክትትሉ በሁለቱም ወረዳዎች በሚገኙ እያንዳንዳቸው ሁለት ጤና ጣቢያዎች፣ ሁለት ጤና ኬላዎች፣ የየወረዳው ጤና ጽሕፈት ቤቶች እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ ወርዶ የተከናወነ ሲሆን፤ በተጨማሪም ከአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል እና ከዞኑ ጤና መምሪያ ጋር በቼክ ሊስት የተደገፈ ግምገማ ተካሂዷል።

‎​በመድረኩ የተገኙት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዛኸኝ ጋሞ፣ የድጋፋዊ ክትትል ቡድኑ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ በመውረድ የጤና ተቋማቱን የአገልግሎት አሰጣጥ እና የኅብረተሰቡን ተጠቃሚነት በአባወራ ደረጃ በአካል ተገኝቶ መመልከቱ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

‎​ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፣ በዞኑ የዜጎችን ጤንነት በመጠበቅ ብሩህ፣ ትጉህ እና አምራች ዜጋን ለመፍጠር በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ ድጋፍ የተደረገባቸው ተቋማት የተለዩትን ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በጥልቀት በመገምገም ለቀጣይ የተሻለ ውጤት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎​የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የጤና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር አዳነ አልቶ በበኩላቸው፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ያካሄደው የተቀናጀ ድጋፋዊ ክትትልና የሰጠው ግብረ መልስ የታዩ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ዕቅድ ውስጥ አካቶ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ትልቅ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

‎​ክትትሉ ከቤተሰብ ደረጃ ጀምሮ የተካሄደ በመሆኑም መምሪያው በቀጣይ አስፈላጊውን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ የጠቆሙት ዶ/ር አዳነ፤ ጤና ኬላዎችን ሙሉ በሙሉ ሥራ ላይ በማድረግ እና ጤና ጣቢያዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ድጋፋዊ ክትትሉ ጥሩ አመላካች መሆኑን ተናግረዋል።

‎​የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የጤናና ጤና ነክ ግብዓት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ሶንቆ በበኩላቸው፣ መሰል የተቀናጁ ድጋፋዊ ክትትሎች በየደረጃው ያሉ የጤና መዋቅሮችን የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻልና የሚታዩ የግብዓት እንዲሁም የአሠራር ክፍተቶችን በቅንጅት ለመፍታት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

‎​በተመሳሳይ ከክልሉ ጤና ቢሮ የመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የድጋፋዊ ክትትሉ ዋና ዓላማ በጤና ሴክተሩ ከተቀመጡት ምሰሶዎች አንጻር የሕዝቡ ተጠቃሚነት የደረሰበትን ደረጃ ማረጋገጥ እና ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ ድጋፍ ማድረግ እንደሆነ አብራርተዋል።

‎​ሥራው በቼክሊስት፣ በምልከታ፣ መረጃዎችን በማጣራትና በማመሳከር በወረዳ ጤና ጽሕፈት ቤቶች፣ በገጠር ጤና ጣቢያዎች፣ በጤና ኬላዎች እና በእያንዳንዱ ተቋም ስር አምስት አምስት አባወራዎችን በማካተት በቤተሰብ ደረጃ መከናወኑ ተገልጿል።

‎በተደረገው ምልከታ የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ በማጠናከር እና የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ በማረም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ጥረት መደረግ እንዳለበት አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

 #ጤናችን |የኩፍኝ በሽታን በጋራ እንከላከል!ልጅዎትን አስቀድሞ በማስከተብ ከክፉኝ በሽታ መከላከል ይቻላል፤ ሆኖም ግን በበሽታ ከተያዙ ወዲያው ህክምና በማግኘት መዳን ይቻላል፤ ነገር ግን ች...
21/10/2026

#ጤናችን |የኩፍኝ በሽታን በጋራ እንከላከል!

ልጅዎትን አስቀድሞ በማስከተብ ከክፉኝ በሽታ መከላከል ይቻላል፤ ሆኖም ግን በበሽታ ከተያዙ ወዲያው ህክምና በማግኘት መዳን ይቻላል፤ ነገር ግን ችላ ካሉ ገዳይ በሽታ ነው! ይጠንቀቁ! ይላል ጤና ቢሮ:

ጥቅምት 11/2019 ጤና ቢሮ ኮሚኒኬሽን
________

🫱 #የኩፍኝ በሽታ ምንድ ነው?

ኩፍኝ በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣና በፍጥነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ነው።

የክፉኝ በሽታ በሕፃና ላይ ከፍተኛ ህመምና ሞት ከሚያስከትሉ ተላላፊ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው።

ወላጆች ልጆቻቸውን በተገቢው የዕድሜ የመከላከያ ክትባት ተከታትለው ማስከተብ አለባቸው።

ኩፍኝ አደገኛና ገዳይ በሽታ ቢሆንም በዋናነት በሽታውን አስቀድሞ ክትባት በመውሰድ መከላከል ይቻላል።

🫱 #የኩፍኝ በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች

🫷 ከፍተኛ ትኩሳትና ሳል፣
🫷 ከፊት ጀምሮ ወደ ሙሉ ሰውነት የሚሰራጭ ሽፍታ፣
🫷 የአፍንጫ ፈሳሽ፣
🫷 የዓይን መቅላትና እንባ ማውጣት ናቸው።

🫱 #መተላለፊያ መንገዶች

🫷 በሳልና በማስነጠስ፣
🫷 በትንፋሽ፣
🫷 በበሽታው ከተያዘ ሰው ከአፍንጫ ወይም ከጉሮሮ ከሚወጡ
ፈሳሾች ጋር ቀጥተኛ ንክኪ ማድረግ፣
🫷 ከአፍና አፍንጫ በሚወጣ ፈሳሽ በተበከሉ ዕቃዎችናቦታዎች ጋር በሚደረግ ንክክ አማካኝነት።

🫱 #መከላከያ መንገዶች

🫷የመጀመሪያው ዙር ክትባት ልጅዎ 9 ወር ሲሞላው፣
ሁለተኛውዙር ደግሞ 15 ወር ሲሞላው ባለመዘናጋት ልጆን
ማስከተብ፣
🫷 በአካባቢዎ በሚካሄዱ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻዎች ላይ ልጆን
ማስከተብ።
🫷 ልጅዎ የኩፍኝ በሽታ ምልክቶችን ካሳየ ሳይዘገዩ ወደ ቅርብ
ጤናተቋም በመውሰድ የህክምና እርዳታ እንድያገኝ ማድረግ።
🫷 በሽታው ወደ ሌሎች ህፃናት እንዳይሰራጭ የታመመውን ልጅ
ምልክቱ ከታየበት ጊዜ ጀምሮ ሽፍታው እስከሚጠፋ ድረስ
ከሌሎች ሰዎች ለይቶ ማቆየትና እረፍት መስጠት።
🫷 ለታመመው ልጅ በቂ ፈሳሽ፣ ጡት፣ ውሃ፣ ገንቢ ምግቦችን
ወዘተ… መመገብ።

ከከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ጋር ለተወለዱ ህፃናት ነፃ የህክምና አገልግሎት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀአርባምንጭ፣ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚ...
20/10/2026

ከከንፈርና ላንቃ ስንጥቅ ጋር ለተወለዱ ህፃናት ነፃ የህክምና አገልግሎት በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል እየተሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ

አርባምንጭ፣ ጥቅምት 10/2019 ዓ.ም (ጋሞ ዞን መ/ኮሚዩኒኬሽን)

ሕክምናው ሁሌም የሚሰጥ ቢሆንም ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 21/2019 ድረስ አለም አቀፍ የፈገግታ ቀን በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአንድ ወር ያህል ከተለያዩ አጋር ድርጀቶች ጋር በመተባበር በዘመቻ መልክ እየተሰጠ እንደሚገኝ የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር አምባቸው ዱማ ተናግረዋል።

በጋሞ ዞንና አካባቢው ያለው ህብረተሰብም ችግሩ ያለባቸውን ህፃናት በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ወደ ሆስፒታሉ በማምጣት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲያደርግ ሥራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።

በሆስፒታለ የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲብ ቀድዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ደስታ ጋልቻ በበኩላቸው አለም አቀፍ የፈገግታ ቀንና ሀገር አቀፍ የፈገግታ ወርን ምክንያት በማድረግ ለበርካታ ህፃናት የህክምና አገልግሎት መስጠቱን ገልጸዋል።
‎
‎ፈገግታ በስነ-ልቦና፣ በአዕምሮ፣ በማህበራዊ ህይወትና መሰል ጉዳዮች ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ያለው በመሆኑ የከንፈር እና የላንቃ ችግር ያለባቸው ህፃናት ህክምናውን አግኝተው መሳቅ እንዲችሉ ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባም ዶ/ር ደስታ አስገንዝበዋል።

ትራስት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሴ ዳቼ በአለምአቀፍ ደረጃ ዘንድሮ ለ27ኛ እንዲሁም በሃገራችን ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለም አቀፍ የፈገግታ ቀን ምክንያት በማድረግ በሃገራችን 6 ማዕከላት ለአንድ ወር ያህል የሚቆይ ነፃ የህክምና አገልግሎት በዘመቻ መልክ እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አንዱ ማዕከል አርባምንጭ ሆስፒታል መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ በሆስፒታሉ ከ50 በላይ ለሚሆኑ ችግሩ ላለባቸው ህፃናት ህክምናውን ለመስጠት መታቀዱንም ጠቁመዋል።

እስካሁን በነበረው ቆይታም 13 ያህል ህፃናት ህክምና ማግኘታቸውን የገለፁት አቶ ደሴ ትራስት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ማህበር ስማይል ትሬን ከተሰኘ ኢንተርናሽናል ግብረሰናይ ድርጀት ጋር በመሆን ለህፃናቱ ከሚሰጠው ከነፃ የህክምና አገልግሎት በተጨማሪ ለአስታማሚ ቤተሰቦችም የትራንስፖርት፣ የምግብና ተያያዥ ወጪዎች እንደሚሸፈኑ ተናግረዋል።

በዚህ ዘመቻ ወቅት እንደ ሃገር ከ3 ሺህ በላይ ችግሩ ላለባቸው ህፃናት ህክምና ለመስጠት መታቀዱ የተገለፀ ሲሆን እስካሁንም ከ160 በላይ ህፃናት መታከም መቻላቸው ተገልጿል።

ችግሩ ያለባቸው የህፃናት ወላጆችም ሆኑ አጠቃላይ ህብረተሰብ ክስተቱ ከብዙ ህፃናት መካከል ጥቂቶችን የሚያጋምና በህክምና የሚድን መሆኑን በመገንዘብ በችግሩ ከመሸማቀቅና ህፃናትን ከመሸሸግ ይልቅ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ የበኩሉን ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

  🙏
20/10/2026

🙏

👉   መንስኤና መከላከያ መንገዶች: ጤና ቢሮዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ በብዛት የሚከሰትና ለሕይወት አስጊ ሊሆን የሚችል የሳንባ ኢንፌክሽን ነው። በሽታው የሕፃናቱን የአየ...
20/10/2026

👉 መንስኤና መከላከያ መንገዶች: ጤና ቢሮ

ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ላይ በብዛት የሚከሰትና ለሕይወት አስጊ ሊሆን የሚችል የሳንባ ኢንፌክሽን ነው።

በሽታው የሕፃናቱን የአየር ከረጢቶች በፈሳሽ ወይም በመግል ስለሚሞላ መተንፈስ አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል።

የሳንባ ምች በተለያዩ በአይን በማይታዩ ረቂቅ ተሕዋስያን (ጀርሞች) አማካኝነት ይከሰታል። ከ5 ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት ላይ የከፋ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

👉 የሳንባ ምች በሽታ መንስኤዎች

1.ቫይረሶች

በሕፃናት ላይ የሳንባ ምች መከሰት ዋነኛው መንስኤ ቫይረሶች ናቸው። በተለይም Respiratory Syncytial Virus (RSV) እና የኢንፍሉዌንዛ (የጉንፋን) ቫይረሶች በስፋት ያጠቃሉ። በሽታው ብዙ ጊዜ የሚጀምረው ከጉፋን መሰል ምልክቶች ነው።

2.ባክቴሪያዎች (Bacteria)

ባክቴሪያዎች ከባድ የሆነ የሳንባ ምች ሊያስከትሉ ይችላሉ። Streptococcus pneumoniae (ኒሞኮካል) እና Haemophilus influenzae type b (Hib) የተባሉ ባክቴሪያዎች በልጆች ላይ ዋነኞቹ የበሽታው አምጭዎች ናቸው፡፡

3.ፈንገሶች (Fungi)

የበሽታ መከላከል አቅማቸው በጣም ደካማ በሆኑ ህፃናት ለምሳሌ ኤች.አይ.ቪ ባለባቸው ሕፃናት ላይ ሊከሰት ይችላል።

👉 ለበሽታው የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

1. የተመጣጠነ ምግብ እጥረት: በቂ ምግብ ያላገኙ ሕፃናት የበሽታ መከላከል አቅማቸው ስለሚዳከም በቀላሉ ይጠቃሉ።

2. የቤት ውስጥ አየር ብክለት: በቤት ውስጥ የማገዶ እንጨት ወይም የከሰል ጭስ መኖር፤ የሲጋራ ጭስ መኖር።

3. ያለ ዕድሜ መወለድ እና በቂ የክትባት አገልግሎት አለማግኘት።

👉 የሳንባ ምች በሽታ የመከላከያ መንገዶች

1.ክትባትን ማሟላት (Vaccination)

ክትባት በጣም አስተማማኝው መንገድ ነው። ሕፃናት በሀገራችን የክትባት መርሃ ግብር መሠረት የPCV (Pneumococcal Conjugate Vaccine) እና የHib ክትባቶችን፣ እንዲሁም የኩፍኝና የትክትክ ሳል ክትባቶችን በወቅቱ እንዲያገኙ ማድረግ።

2.የእናት ጡት ወተት (Breastfeeding)
ሕፃኑ ከተወለደ ጀምሮ እስከ 6 ወር ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻ መመገብ አለበት። የጡት ወተት የሕፃኑን የተፈጥሮ በሽታ የመከላከል አቅም በእጅጉ ያጠናክራልና።

3.የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት:
ከ6 ወር በኋላ ለሕፃኑ ቫይታሚን ኤ እና ሌሎች አልሚ ምግቦችን ያካተተ የተመጣጠነ ምግብ መስጠት በሽታ የመቋቋም አቅሙን መጨመር።

4.የቤት ውስጥ አየርን ንጹሕ ማድረግ:
ሕፃናት ባሉበት ክፍል ውስጥ የማገዶ ጭስ እንዳይኖር ማድረግ እና ከሲጋራ ጭስ ሙሉ በሙሉ መጠበቅ።

5. ንፅህና መጠበቅ:
የሕፃናትን እጅ አዘውትሮ በሳሙና እና በውሃ ማጠብ፣ እንዲሁም በጉንፋን ወይም በሳል ከተያዙ ሰዎች ማራቅና በሽታው እንዳይዛመት መከላከል ይገባል።

  ዘመን ተመኘን 🙏
20/10/2026

ዘመን ተመኘን 🙏

20/10/2026

Address

Gamo Zone
Arba Minch'

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arbaminch General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share