AmsalechAmanuel.Kachaw

Call Website Contact the business

AmsalechAmanuel.Kachaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from AmsalechAmanuel.Kachaw, Awassa.

NGAT
01/10/2025

NGAT

types of insulin
24/09/2025

types of insulin

Fast fashion is destroying our planet 😢🌍 Every year, millions of tons of clothing waste pollute our soil and water. 😴😴
04/09/2025

Fast fashion is destroying our planet 😢🌍 Every year, millions of tons of clothing waste pollute our soil and water. 😴😴

30/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Noxolo Tyewu, Seble Genene

 #ትክክለኛው አዲሱ የደመወዝ መጠን በእያንዳንዱ ደረጃ የተሸነሸነ 🇪🇹
21/08/2025

#ትክክለኛው አዲሱ የደመወዝ መጠን በእያንዳንዱ ደረጃ የተሸነሸነ 🇪🇹

09/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Cfc Blay, Mariel Sayod Caleza, Hamza Hanif, Amanuel Tagel info

06/08/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Richmond Blay Flavour, Mariel Sayod Caleza, Hamza Hanif, Amanuel Tagel info

05/08/2025

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
_________

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Nursing, Human Nutrition, Optometry, Pediatric and Child Health Nursing, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health, Surgical Nursing, Anesthesia, Psychiatric Nursing, Pharmacy, Medical Radiology Technology, Midwifery, Medicine, Public Health, Medical Laboratory Science and Physiotherapy ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው ከነሀሴ 7 - 9/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ መሆኑን እየገለጽን ለተጨማሪ መረጃ የጤና ሚኒስትር ቴልግራም ቻናል() ይመልከቱ።

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia

😱ጥሬ ስጋ የምትበሉ ሰዎች ግን የኮሶ ትል ይሄንን እንደሚመስል አስባችሁ ታውቃላችሁ?  😱  በዚያ አፍን በምራቅ የሚሞላ፣ ጥሬ ስጋ ወይም በቅቤ የሚያብለጨልጭ ክትፎ ውስጥ ተደብቀው፣ የሚጠባበ...
05/08/2025

😱ጥሬ ስጋ የምትበሉ ሰዎች ግን የኮሶ ትል ይሄንን እንደሚመስል አስባችሁ ታውቃላችሁ? 😱

በዚያ አፍን በምራቅ የሚሞላ፣ ጥሬ ስጋ ወይም በቅቤ የሚያብለጨልጭ ክትፎ ውስጥ ተደብቀው፣ የሚጠባበቁ ጭራቅ መሰል ተውሳኮችን ምስል ላስተዋውቃችሁ 😄

1️⃣.የበሬ ሥጋ ኮሶ (Taenia Saginata)🥩
👉 ምንጭ:- ያልበሰለ የከብት ስጋ
👉 በትንሹ አንጀትዎ ውስጥ፣ ተጣብቆ ይኖራል
👉እስከ 15 ሜትር የሚደርስ አስፈሪ ርዝመትሊኖረው ይችላል!

2️⃣.የአሳማ ሥጋ ኮሶ (Taenia Soleum)🐷
👉መነሻ፡ ያልበሰለ የአሳማ ሥጋ
👉የሚያጠቃው ፡ አንጀት፣ ጡንቻዎች፣ እንዲሁም አንጎል (በሳይስቲከርኮሲስ) ውስጥ መኖሪያውን ሊያደርግ ይችላል
👉እስከ 7 ሜትር (23 ጫማ) የሚደርስ ርዝመት ሊኖረው ይችላል
3️⃣.የአሳ ኮሶ ትል(Diphyllobothrium latum (Fish Tapeworm) 🐟
👉መነሻ፡ ጥሬ ወይም በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ አሳ
👉የሚያጠቃው፡ አንጀትን ፣
👉እስከ 12 ሜትር (39 ጫማ) ሊረዝም ይችላል

4️⃣.የውሻ ትል(Echinococcus granulosus) 🐶
👉መንሻ ፡ ከተበከለ ውሻ ጋር ንክኪ ወይም የተበከለ አፈር/ውሃ
👉የሚያጠቃው ፡ ጉበት፣ ሳንባ
👉ጥቃቅን ግን አደገኛ ነው ፣ ከ 2-7 ሚ.ሜ ብቻ ይረዝማል
5️⃣.ሃይሜኖሌፒስ ናና (ድንክ ትል) 🐀
👉መነሻ፡ በተበከሉ ምግቦች ወይም በተበከለ እጅ በመመገብ
👉የሚጎዳው፡ አንጀትን
👉እስከ 2 ሜትር (6.5 ጫማ) የሚያድግ ተንኮለኛ ተንቀሳቃሽ

😨 ሥጋ እና አሳን በደንብ ያብስሉ፣ እጅዎን በጥንቃቄ ይታጠቡ፣ የታከመ ውሃ ብቻ ይጠቀሙ ። 💥

#የኮሶትል #የጤናትምህርት #እጅመታጠብ #ቁርጥ #ክትፎ #የጤናግንዛቤ #የቁርጥአፍቃሪዎች
#ስጋ #ጥሬስጋ
#ጠቃሚምክሮች

 #የህመም-ማስታገሻዎች-መዘዝ ዶ/ር ጌታሁን ወዳሎብዙ ሰዉ የህመም ማስታገሻ በተለይም Ibuprofen እና Diclofenac የተባሉ መድኃኒቶችን ጉዳቱን ሳያዉቅ እየወሰደ መሆኑን ስላስተዋልኩ ...
02/08/2025

#የህመም-ማስታገሻዎች-መዘዝ
ዶ/ር ጌታሁን ወዳሎ

ብዙ ሰዉ የህመም ማስታገሻ በተለይም Ibuprofen እና Diclofenac የተባሉ መድኃኒቶችን ጉዳቱን ሳያዉቅ እየወሰደ መሆኑን ስላስተዋልኩ ትንሽ ነገር በመስጠት የሙያ ግዴታዬን ለመወጣት ወደድኩ። መልካም ንባብ 🇪🇹

የህመም ማስታገሻ ማለት ስንታመም የሚረብሸንን የህመም ስሜት በጊዜያዊነት ለማስታገስ የሚረዳ መድኃኒት ነዉ። የህመም ማስታገሻ የህመም ስሜቱን እንጂ በሽታዉን አያክምም። ለምሳሌ :ወባ ብይዘን ትኩሳት፣ ራስ ምታትና ሌሎች የህመም ስሜቶች ይሰማሉ፤ ይረብሻሉ። የህመም ማስታገሻ እነዚህን ትኩሳት፣ ራስ ምታት ያሉ ምልክቶችን እንጂ ያስከተለዉን ወባ አያክምም፤ በጊዜያዊነት ሊያስታግሱ ይችላሉ ግን ወባ እስካልታከመ ድረስ እነዚህ ስሜቶች ዳግም መነሳታቸዉ አይቀርም። ስለዚህም ህመሙን ማስታገስ አስፈላጊ ቢሆንም በሽታዉን በአግባቡ እየታከሙ እሱንም የሚፈቀደዉን መጠን መሆን አለበት። ያ ካልሆነና ያለአገባብና ከሐኪም ትዕዛዝ ዉጪ የሚንወስድ ከሆነ ሰዉነታችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ።
ከሚያደርሱት ጉዳትም ጥቅቶቹን እነሆ 👇

✅ጨጓራ እና አንጀት
👉ብዙ የህመም ማስታገሻዎች በተለይም NSAID ስር የሚመደቡ እነ Ibuprofen የጨጓራ ቁስለት ህመም ህመም አልፎም ቁስለት እና መድማት ሊያደርሱ ይችላሉ።
✅ጉበት
Acetaminophen የተባለ መድኃኒት በፋብሪካ ስሞች paracetamol,paramol,panadol...ተብሎ የሚጠራዉ የህመም ማስታገሻ ከሚፈቀደዉ መጠን በላይ (overdose) ከተወሰደ ጉበት ላይ ጉዳት ያደርሳል። በተለይም አልኮል ተጠቃሚ ከሆኑ።
✅ኩላሊት
Ibuprofen,Diclofenac እና ሌሎች NSAID ቡድን የሚመደቡ የህመም ማስታገሻዎችን ለረጅም ጊዜ ወይም ከሚፈቀደዉ መጠን በላይ መዉሰድ ኩላሊት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
✅ልብ እና ደም ስር
NSAID(Ibuprofen,naproxene,Diclofenac...) ዓይነት የህመም ማስታገሻዎች ተደጋጋሚ ከተወሰዱ የደም ግፊት መጨመር፣ የልብ ደምስር መዘጋት አደጋ እና ስትሮክ(Stroke) ያስከትላሉ።

✅የመድኃኒት ሱሰኝነት
Opoid የሚባል ቡድን ዉስጥ የሚካተቱ እነ Pethidine,Tramadol,Morphine, codein, methadone... የህመም ማስታገሻዎች የመድኃኒት ሱሰኝነት ያስከትላሉ። እነዚህን መድኃኒቶችን አንዳንድ ሰዎች 'ሞቅ' ለማለትም ከመዉሰዳቸዉ የተነሳ ከመጠን በላይ ወስደዉ ለሞት ይደርሳሉ። እንዲሁም ብዙ ሰዉ Tramadol የተባለ መድኃኒት ሱሰኛ እየሆነ ስለሆነ ይህ መድኃኒት ያለሐኪም ትዕዛዝ እንዳይሸጥ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር መመሪያ መስጠቱ የሚታወስ ነዉ።

✅የፈዉስ ህክምና የሌላቸዉ በሽታዎች ለረጅ ጊዜ የህመም ማስታገሻ መድኃኒት ልታዘዝ ይችላል። ይህም ሐኪሙ በሽታዉን ለይቶ፣ ፈዉስ ህክምና እንደለሌ አረጋግጦ እንዲሁም የህመም ማስታገሻ መድኃኒቱ ጥቅሙንና ጉዳቱን አመዛዝኖ ይወስናል።

😢ኦቶና ሆስፒታል

👉ሚታየንን እሾህ እያነሳን ጉዟችን እንቀጥል!

👉ዶ/ር ጌታሁን ወዳሎ(የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ሐኪም)

ጣሊያን በወሲብ ወንጀለኞች ላይ  የኬሚካል castration ሕክምናን ለመተግበር ረቂቅ ህግ አቀረበች👉የቀረበው ረቂቅ ህግም ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል ተብሏል።የጣሊያን መንግስት በደፋሪዎች እ...
02/08/2025

ጣሊያን በወሲብ ወንጀለኞች ላይ የኬሚካል castration ሕክምናን ለመተግበር ረቂቅ ህግ አቀረበች

👉የቀረበው ረቂቅ ህግም ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል ተብሏል።

የጣሊያን መንግስት በደፋሪዎች እና በህፃናት በደል ፈጻሚዎች ላይ የኬሚካል castration ሕክምና እንዲሰጥ የሚያስችል ረቂቅ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብና ክርክር እየተካሄደ ነው።

ይህ ሃሳብ፣ ሕክምናው በይፋ ተፈጻሚ ለመሆን የቀረበ ረቂቅ እንጂ የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልሆነ ታውቋል።

የቀረበው ረቂቅ ህግ የኬሚካል castrationን እንደ አማራጭ ቅጣት የሚመለከት ሲሆን፣ ወንጀለኞች በፈቃደኝነት ሕክምናውን ከተቀበሉ የእስር ጊዜያቸውን እንዲቀንስላቸው ያስችላል።

ሕክምናው ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ አይደለም። በልዩ መርፌዎች ወይም መድኃኒቶች አማካኝነት የወንድ ሆርሞን (testosterone) ምርትን በመቀነስ የወሲብ ፍላጎትን ለጊዜው የሚያግድ ሲሆን፣ መድኃኒቱ ሲቆም ግን ውጤቱ ይገለበጣል ተብሏል።

ይህ ቅጣት በዋነኛነት ውጤታማ ይሆናል ተብሎ የሚታሰበው፣ ወንጀለኛው ከእስር ከተለቀቀ በኋላ ሕክምናውን በየጊዜው እንዲከታተል በሚያስገድድ ጠንካራ የክትትል ስርዓት ነው ተብሏል።

በዚህ ስርዓት መሰረት፣ ወንጀለኛው ለምሳሌ በየሶስት ወሩ ወደ ተቋም በመሄድ መርፌውን መውሰድ ግዴታ ይሆንበታል ነው የተባለው።

የቅናሽ የተደረገው የእስር ጊዜም በሕክምናው ቀጣይነት ላይ የተመሰረተ ነው የተባለ ሲሆን፤ወንጀለኛው በፈቃደኝነት የገባውን ስምምነት በመጣስ ሕክምናውን ካቋረጠ፣ ቀሪ የእስር ጊዜውን ለመፈጸም ወደ ወህኒ ቤት የመመለስ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚችል ረቂቅ ህጉ ያመለክታል።

የዚህ ረቂቅ ህግ ደጋፊዎች የወሲብ ወንጀል ድግግሞሽን ለመቀነስና የህብረተሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ ሲገልጹ፣ ተቃዋሚዎች ግን የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው በማለት እና በሀገሪቱ ህገ-መንግስት ላይ ያለውን ተፈጻሚነት በመጠራጠር ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው።

የረቂቅ ህጉ እጣ ፈንታም በጣሊያን ፓርላማ ውስጥ ባለው ክርክርና ውሳኔ ላይ የተንጠለጠለ ይሆናል ነው የተባለው።

የቀረበው ረቂቅ ህግ ከጸደቀና ተግባራዊ መሆን ከጀመረ፤ወንጀለኛው የእስር ጊዜየ ይቀነስልኝ፤ድጋሚ ወሲብ እንዳልፈጽም የሚያስችለውን ኬሚካል በፈቃደኝነት እወስዳለሁ በማለት ኬሚካሉን ወስዶ ከእስር መለቀቅ ይችላል ተብሏል።

ወንጀለኛው ኬሚካሉን ከወሰደው የወሲብ ፍላጎቱ እንዲጠፋ እና ለወሲብ እንዳይነሳሳ ያደርገዋል ነው የተባለው።

ረቂቅ ህጉ በፓርላማ ውስጥ ውይይት እየተደረገበት በመሆኑ፣ የመጨረሻ ውሳኔ እስካሁን እንዳልተላለፈም ተመላክቷል።

የኬሚካል castration ሕክምናን ለወሲብ ወንጀለኞች እንደ ቅጣት ወይም የሕክምና አካል አድርገው የሚጠቀሙ በርካታ ሀገራት እንዳሉ የተመላከተ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አሜሪካ በአንዳንድ ግዛቶች (ለምሳሌ ካሊፎርኒያ፣ ፍሎሪዳ፣ አይዋ)፤ደቡብ ኮሪያ፤ ፖላንድ፤ ሩሲያ፤ ኢንዶኔዥያ፤ ዩናይትድ ኪንግደም፤ ማዳጋስካር ተጠቃሽ ናቸው ተብሏል።

Address

Awassa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when AmsalechAmanuel.Kachaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to AmsalechAmanuel.Kachaw:

Shortcuts

Share