Medical Information

Call Directions Website Contact the business

Medical Information በዚህ ገጽ ጤናን የተመለከቱ የሥራ ማስታወቂያዎች፤ ሕይወታዊ ቁም-ነገሮችና አጠቃላይ መረጃዎችን እንለዋወጥበታለን! Medical Media

🚀  Africa CDC 𝐢𝐬 𝐡𝐢𝐫𝐢𝐧𝐠!We're recruiting digital health and data professionals through the Africa Volunteers Health Corp...
10/10/2026

🚀 Africa CDC 𝐢𝐬 𝐡𝐢𝐫𝐢𝐧𝐠!

We're recruiting digital health and data professionals through the Africa Volunteers Health Corps (AVoHC) to support the 𝐄𝐛𝐨𝐥𝐚 𝐫𝐞𝐬𝐩𝐨𝐧𝐬𝐞 𝐢𝐧 𝐭𝐡𝐞 𝐃𝐑𝐂. Six roles are open in Kinshasa and the provinces (see the graphic).

⏰ 𝐃𝐞𝐚𝐝𝐥𝐢𝐧𝐞: 𝟏𝟑 𝐎𝐜𝐭𝐨𝐛𝐞𝐫, 𝟐𝟑:𝟓𝟗 𝐄𝐀𝐓

👉 Apply: https://lnkd.in/du7SGg7V

Please share! 🌍

ዶ/ር ሙሉቀን አርጋው፣ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ፣ እና ወ/ሮ ሳሕረላ ዐብዱላሒ የጤና ሚኒስቴር ዴዔታ ኾነው ተሾመዋል።
10/10/2026

ዶ/ር ሙሉቀን አርጋው፣ ወ/ሮ ፍሬሕይወት አበበ፣ እና ወ/ሮ ሳሕረላ ዐብዱላሒ የጤና ሚኒስቴር ዴዔታ ኾነው ተሾመዋል።

09/10/2026

What is optogenetics?

ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በድጋሜ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኾነው በመሾማቸው መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን!Ministry of Health,Ethiopia
08/10/2026

ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በድጋሜ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ኾነው በመሾማቸው መልካም የሥራ ዘመን እንመኝላቸዋለን!
Ministry of Health,Ethiopia

ከሚያስገርሙኝ ሀኪሞች - ዶ/ር ዳዊት አሰፋበፊት በፊት ስፔሻላይዝ ለማድረግ የተወሰኑ አመታት በመንግስት ሆስፒታል ማገልገል ግዴታ ነበር። የገጠር ሆስፒታል ከሆነ ሁለት አመት፣ ትልቅ ከተማ ከ...
08/10/2026

ከሚያስገርሙኝ ሀኪሞች - ዶ/ር ዳዊት አሰፋ

በፊት በፊት ስፔሻላይዝ ለማድረግ የተወሰኑ አመታት በመንግስት ሆስፒታል ማገልገል ግዴታ ነበር። የገጠር ሆስፒታል ከሆነ ሁለት አመት፣ ትልቅ ከተማ ከሆነ አራት አመት፣ አዲስአበባ ከሆነ ደግሞ አምስት አመት።

ዶ/ር ዳዊት አሰፋ የአማኑኤል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ በነበረበት ወቅት አራት የአእምሮ ህክምና ስፔሻላይዝ ለማድረግ ያሰቡ ከተለያየ ቦታ የመጡ ጠቅላላ ሀኪሞች "እኛ አማኑኤል ሆስፒታል አልሰራንም ነገር ግን የአእምሮ ህክምና መማር እንፈልጋለን።" ይሉታል።

በፈገግታ "እንዴ ሳይካትሪ የሚማር ተገኝቶ ነው እንዴ?" ብሎ ሆስፒታሉ ስፖንሰር እንዲያደርጋቸው ወዲያውኑ ለሰው ሀብት ደብዳቤ ይፅፍላቸውና በሳይካትሪ ስፔሻላይዝ ያደርጋሉ። ይህንን ነገር በደንብ የማስታውሰው ከአራቱ ጠቅላላ ሀኪሞች አንዱ እኔ ስነበርኩ ነው።

ዶ/ር ዳዊት ብዙ የሚያስገርሙኝ ባህሪዎች አሉት ነገር ግን ለዛሬ ለኔ ጎላ ብለው የታዩኝን አራቱን ብቻ ላጋራችሁ።

1) ከታካሚዎችም ከስራ ባልደረቦቹንም ጋር ሲነጋገር በተረጋጋ ሁኔታ በጥሞና የሚያዳምጥበት መንገድ ያስገርመኛል።

2) ሰዎች እንዲማሩ ረጅም ርቀት በመሄድ ሁኔታዎችን ያመቻቻል። አማኑኤል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ በነበረበት ጊዜ በጣም ብዙ ሰዎች እንዲማሩ በማበረታታት፣ አንዳንዴ executive ውሳኔ በማሳለፍ ጭምር ብዙዎች እንዲማሩ አግዟል። ለትምህርት ያለው አዎንታዊ አመለካከትና መማር የሚፈልጉ ሰዎችን ለማገዝ ያለው ቅንነት ይገርመኛል።

3) ለኪነ ጥበብ ያለው ፍቅር። ዶ/ር ዳዊት ብዙ መፃህፍት ስላነበበ ስለመፃህፍት ሲያወራ አፍ ያስከፍታል። የአማኑኤል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ በነበረት ወቅት እነማህሙድ አህመድ ጭምር የተሳተፉባቸውን ሁለት ትልልቅ ኮንሰርቶች አማኑኤል ሆስፒታል ውስጥ እንዲቀርብ አድርጓል።

"ጉዞ ለአእምሮ ጤና" የሚል ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ ሲደረግ "ሞጋች" የተባለ ቲያትር በክልል ከተሞች እንዲታይ፤ በጎዳና ላይ ያሉ የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች ከጎዳና ተነስተው፣ ታጥበው ህክምና እንዲያገኙ አድርጓል።

በየክልሉ ያሉ 'የሚመለከታቸው አካላት' ለአእምሮ ጤና ትኩረት እንዲሰጡ በሆስፒታሎች የአእምሮ ህክምና ዋርዶች እንዲከፈቱ በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በቅርቡ ደግሞ "የሁሉ" የተባለውን ውብ ረጅም ልቦለድ ፅፎ አስነብቦናል።

4) እኔን በጣም የሚያስገርመኝ ግን ለሀገር ያለው ፍቅር እና የሀገራችን የአእምሮ ጤና እንዲሻሻል ያለው ትልቅ ሀገራዊ ራእይ ነው። ያለው ራዕይ በጊዜ የተወሰነ ቅፅበተኛ፣ በቦታ የተወሰነ ቁንፅል ግብ ሳይሆን ሁሉንአቀፍ (Comprehensive) እና ነገን አሻግሮ የሚመለከት (Foresighted) ራእይ ነው።

"የሁሉ" መፅሀፉ ላይ ስለሀገራችን የግጭት እሽርክርክሪት፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ ስለሚተላለፍ የስነ ልቦና ጠባሳ የዳሰሰበት ፅሁፍ የሀገር ጉዳይ ምን ያህል እንዲያሳስበው በግልፅ የሚያሳይ ነው። በተግባርም ደግሞ የኢትዮጲያ የአእምሮ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዲቋቋም እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥረት እንዳደረገ የምናውቅ ሰዎች እናውቃለን።

የምታውቁት ጨምሩበት...

ዶ/ር ዳዊት ለአማኑኤል ሆስፒታል ላደረገው አስተዋፅኦ አንድ ዋርድ ቢሰይምለት አይበዛበትም።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!!!!
Mental Wellness የአእምሮ ጤና

የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን (PPSOE) ኢትዮጵያ መስራችና አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ክብራ ከበደ፣ ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን እና እንቅስቃሴ መታወክ ማህበር (Internation...
07/10/2026

የፓርኪንሰን ፔሸንትስ ሰፖርት ኦርጋናይዜሽን (PPSOE) ኢትዮጵያ መስራችና አማካሪ የሆኑት ወይዘሮ ክብራ ከበደ፣ ዓለም አቀፍ የፓርኪንሰን እና እንቅስቃሴ መታወክ ማህበር (International Parkinson and Movement Disorder Society) የ2026 የህዝብ አገልግሎት ሽልማት (Public Service Award) ተሸላሚ ሆነዋል።

ወይዘሮ ክብራ በሀገራችን ብቸኛውን የፓርኪንሰን ህሙማን መርጃ ድርጅት በማቋቋም ላለፉት 15 ዓመታት በርካታ የፓርኪንሰን ህሙማንን ተጠቃሚ ያደረጉ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውነዋል።

በዋናነትም የግንዛቤ ፈጠራ፣ የአቅም ግንባታ እንዲሁም የድጋፍና እንክብካቤ ሥራዎችን ሲሠሩ ቆይተዋል።
ራሳቸውም የፓርኪንሰን ታማሚ የሆኑት ወይዘሮ ክብራ፣ ላለፉት 26 ዓመታት ከበሽታው ጋር እየኖሩ ይገኛሉ።

በሽታው እንቅስቃሴን የሚያውክ እና ለከፍተኛ የእንቅስቃሴ መታወክ የዳረጋቸው ቢሆንም፣ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እና ለህሙማን የሚደረጉ ድጋፎችን እንዳያደርጉ አላገዳቸውም።

በወይዘሮ ክብራ ጽናትና አመራር የተመሰረተው ድርጅቱ፣ ዛሬ ላይ 1,200 የፓርኪንሰን ህሙማን እና 745 አስታማሚዎችን በአባልነት በመመዝገብ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል።

የፓርኪንሰን ህመም 85 በመቶ የሚሆነውን ከ60 ዓመት በላይ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ ቢሆንም፣ ቀሪው 15 በመቶ ከ60 ዓመት በታች ያሉትን ያጠቃል። ወይዘሮ ክብራም ከእነዚህ 15 በመቶ ውስጥ አንዷ ሲሆኑ፣ በ31 ዓመታቸው በበሽታው ተይዘው ከህመሙ ጋር በተያያዘ ተገቢ ህክምና ባለማግኘት እና ከበሽታው ምልክት ጋር ተያይዞ ለከፍተኛ መገለልና ችግር ተጋልጠው ነበር።

መሰረቱን በአሜሪካ ያደረገው International Parkinson and Movement Disorder Society ከፓርኪንሰን እና ሌሎች ከእንቅስቃሴ መታወክ ጋር ተያያዥነት ባላቸው ህመሞች ላይ በርካታ ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ጥናትና ምርምር ሥራዎችን ማከናወን ዋና ትኩረቱ ነው። ማህበሩ የዘንድሮ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን በደቡብ ኮሪያ እያካሄደ ይገኛል።

ይህ የተከበረ ዓለም አቀፍ ሽልማት ለወይዘሮ ክብራ ከበደ መሰጠቱ፣ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የፓርኪንሰን ህሙማን የተደረገ ትልቅ እውቅና እና ታሪካዊ ምዕራፍ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡ www.parkinsonethiopia.org

06/10/2026

🦠⚠️በጎረቤት ኬንያ የመጀመሪያው የኢቦላ በሽታ ታማሚ ትናንት ሕይወቱ አለፈ። ኬንያዊው ሟች፣ ዲሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ውስጥ ለዓመታት ይኖር እንደነበርና በአገሪቱ ሆስፒታሎች ሲታከም እንደቆየ ተናግረዋል። ሟቹ፣ ኬንያ ውስጥ በኢቦላ በሽታ በመያዝም ሆነ በበሽታው በመሞት የመጀመሪያው ስው ነው። የኬንያ የጤና ሚንስቴር ባለሥልጣናት፣ የሟቹን ቤተሰቦችና የሕክምና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከግለሰቡ ጋር አካላዊ ንክኪ የነበራቸውን 28 ሰዎች ለይተዋል። ከግለሰቡ ጋር በአውሮፕላን ወደ ኬንያ የገቡ 23 ሰዎችን የማፈላለግ ጥረት እንደቀጠለ ነው ተብሏል። ኬንያ፣ ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገራት ኢቦላ የተገኘባት የመጀመሪያዋ አገር ናት።

Congratulations to Professor Solomon and the entire DepGenAfrica team on receiving the Pamela Sklar Innovation Award at ...
06/10/2026

Congratulations to Professor Solomon and the entire DepGenAfrica team on receiving the Pamela Sklar Innovation Award at the WCPG 2026 Annual Conference in Glasgow, Scotland. 🎉
This is a remarkable recognition of their work advancing psychiatric genetics research in African populations, including Ethiopia, Malawi, and Nigeria.
A proud moment for Ethiopian research and an inspiring achievement for global mental health research. 🇪🇹👏

St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMCበቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Med...
06/10/2026

St. Paul's Hospital Millennium Medical College-SPHMMC

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁ የመጨረሻ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ፦

Medicine:https://sphmmc.edu.et/2026/medicine_2029_final.pdf

Comprehensive Nursing:https://sphmmc.edu.et/2026/nursing_2019_final1.pdf

የመግቢያ ቀን በቅርቡ ይገለጻል ተብሏል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medical Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Medical Information:

Shortcuts

Share