Alamura Primary Hospital , Hawassa

Directions

Alamura Primary Hospital , Hawassa Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Alamura Primary Hospital , Hawassa, Medical and health, Awassa.

ዛሬ በቀን 1/01/19 ዓ.ም የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማናጅመንትና የስራ አስተባባሪዎች ከተረኛ ባለሙያዎች ጋር በዛሬው እለት የአዲስ አመት በአልን በጋራ አክብረዋል።
11/09/2026

ዛሬ በቀን 1/01/19 ዓ.ም የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማናጅመንትና የስራ አስተባባሪዎች ከተረኛ ባለሙያዎች ጋር በዛሬው እለት የአዲስ አመት በአልን በጋራ አክብረዋል።

🕊🌻🌻🌻️🌻🌻 🕊እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!ውድ የአላሙራ  ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት በሙሉ፤በቅድሚያ  እንኳን ለአዲሱ ዓመት ...
11/09/2026

🕊🌻🌻🌻️🌻🌻 🕊
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

ውድ የአላሙራ ሆስፒታል የሕክምና ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች እና የማኔጅመንት አባላት በሙሉ፤

በቅድሚያ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ እላለሁ!

በተጠናቀቀው ዓመት ለታካሚዎቻችን ጤና እና ደኅንነት ስትሉ ቀንና ሌሊት ላሳያችሁት አስደናቂ ትጋት፣ ሩኅሩኅነት እና ሙያዊ ሥነ-ምግባር ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ተቋማችን ከጤና ጣቢያ ወደ ሆስፒታል ባደገበት በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ የሕዝብ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ ሆስፒታል እንዲሆን ያደረጋችሁት አስተዋጽኦ እጅግ የሚኮራ ነው።

በተለይም ከዕለት ተዕለት የሕክምና አገልግሎታችሁ ባሻገር፣ ከደመወዛችሁ እያዋጣችሁ እና ጊዜያችሁን ሰውታችሁ በክረምቱ የበጎ ፈቃድ ሥራ እና ዓመቱን ሙሉ ስታከናውኑት ለነበረው ማኅበረሰብ አቀፍ የሰብዓዊነት ሥራ (የደም ልገሳ፣ የነጻ ሕክምና፣ ለአቅመ ደካሞች የተደረገ ድጋፍ) የላቀ ክብር ይገባችኋል። እናንተ የሙያ ብቻ ሳይሆን የሰብዓዊነትም ጀግኖች ናችሁ!

አዲሱ ዓመት የጀመርነውን የለውጥ እና የዕድገት ጉዞ አጠናክረን የምንቀጥልበት፣ ሆስፒታላችንን ይበልጥ ለታካሚዎች ምቹ እና የላቀ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ በጋራ የምንተጋበት የውጤት ዘመን እንደሚሆን ሙሉ እምነቴ ነው።

እግዚአብሔር አዲሱን ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የብልጽግና እና የትብብር ዓመት እንዲያደርግልን የሁልጊዜ ፀሎቴ ነው። ለእስናንተም ሆነ ለቤተሰቦቻችሁ ያሰባችሁት መልካም ነገር ሁሉ የሚሳካበት ብሩህ ዘመን ይሁን!

መልካም አዲስ ዓመት! 🌼🎉

አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አድሶ ለባለቤቱ አስተላለፈ።*********************************** አላሙራ የመ...
10/09/2026

አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አድሶ ለባለቤቱ አስተላለፈ።
***********************************
አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት አድሶ ለባለቤቱ አስተላልፏል።

ሆስፒታሉ ከባለሙያዎች ወርሀዊ መዋጮ ያደሰውን ቤት የታቦር ክፍለከተማ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ሀርባጮ፣ የጤና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ ወ/ሮ ትዕግስት እሳቱ፣ የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም የሆስፒታሉ ማናጅመንትና የMCC ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ቁልፍ አስረክቧል።
የታቦር ክፍለከተማ አስተዳዳሪ አቶ ግርማ ሀርባጮ በንግግራቸው ሆስፒታሉ በሁሉም አፈጻጸም በላቀ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በተለይም በመድሃኒት አቅርቦት ከማህበረሰቡ አዎንታዊ አስተያየት እንዳለ ገልፀው በበጎ አገልግሎትም ሆስፒታሉ የሚያከናውናቸው ተግባራት ጎልተው እንደሚታዩ አንስተዋል።
የጤና መምሪያ ሀላፊ ተወካይ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት እሳቱ በበኩላቸው በMCC ተግባራት፣በቤተሰብ ጤና ቡድን፣palliative care እንዲሁም በበጎ ተግባራት መልካም ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አስታውሰው ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአፀንኦት አሳስበዋል። በዚህ በጎ ተግባር ላይ የተሳተፉ ባለሙያዎችንም አመስግነዋል።

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ዩዌ የሆስፒቲሉ MCCቲም ባለሙያዎች በተቋሙ በርካታ የበጎነት ተግባር እንደሚያከናወኑ ገልጸው ፤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ታድሶ ለባለቤቱ የማስተላለፍን ጨምሮ እገዛ ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች የእህልና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ እጅግ አበረታች ነው ብለውታል ፡፡

በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሆስፒታሉ የደም ልገሳ፣የደም ግፊት፣ የስኳር፣ የሳንባ ነቀርሳ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር፣ የጡት ካንሰር፣ የአዕምሮ ህመም፣ የአይን ህመም እንዲሁም የህፃናት የምግብ እጥረት ልየታና ህክምና አገልግሎቶች ማጠቃለያ አከናውኗል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የዘመን መለወጫ በዓልን እና የክረምት በጎ አገልግሎት ማጠቃለያን ምክንያት በማድረግ በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው   ማ...
09/09/2026

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የዘመን መለወጫ በዓልን እና የክረምት በጎ አገልግሎት ማጠቃለያን ምክንያት በማድረግ በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በተዘጋጀው ማዕድ ማጋራት ፕሮግራም ላይ በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
**************************************
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ የ2019 ዓም የዘመን መለወጫ በዓሉን እንዲሁም የክረምት በጎ አገልግሎት ማጠቃለያን አስመልክተው በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመገኘት በሆስፒታሎቹ የተዘጋጀውን ማዕድ አጋርተዋል።

በ MCC ኮሚቴ አስተባባሪነት ከስታፍ በተሰበሰበ መዋጮ በተዘጋጀው በአል ላይ ከ 100 በላይ ለሚሆኑ በቀበሌያችን የድሀድሀ ተብለው ለተለዩ አቅመደካሞች የዘይትና ዱቄት ድጋፍ ተደርጓል።
እንዲሁም ከ60 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በጤናው ዘርፍ በትጋት፣ በቁርጠኝነትና በመሰጠት ማኅበረሰቡን ለሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችና ሠራተኞች ምስጋና አቅርበዋል።

ዶ/ር ሰላማዊት የሕብር ቀን የብዝሃነት ውበትን፣ የአብሮነትንና የሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን የሚያጎላ በዓል መሆኑን ጠቁመው፣ እነዚህ እሴቶች በተግባር እንዲጎለብቱ ሰው ተኮር የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

በዕለቱም የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ዮዌ በዚህ መልካም ተግባር ላይ ከወር ደመወዛቸው መዋጮ በማድረግ ለተሳተፉት የሆስፒታሉ ስታፍ እንዲሁም ዝግጅቱን በማቀናጀት የተሳካ እንዲሆን ላደረጉት ለMCC ኮሚቴ አባላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን እንዲ ያለው በጎ ተግባር በቀጣይነትም እንደሚካሄድ ቃል ገብተዋል።
በመጨረሻም ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት ደስታቸውን በመግለፅ የሆስፒታሉንም ሰራተኞች አመስግነዋል።

የ2018 ዓ.ም. የጤና ኤክስቴንሽንና የቤተሰብ ጤና ቡድን አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ*********************************በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም. የ...
27/08/2026

የ2018 ዓ.ም. የጤና ኤክስቴንሽንና የቤተሰብ ጤና ቡድን አፈጻጸም ግምገማ ተካሄደ
*********************************
በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2018 ዓ.ም. የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምና የቤተሰብ ጤና ቡድን አፈጻጸም ዓመታዊ ግምገማ ተካሄደ።
በግምገማው የ2018 ዓ.ም. አጠቃላይ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አፈጻጸም፣ የቤተሰብ ጤና ቡድን የሥራ አፈጻጸም እንዲሁም በሆስፒታሉ ማኔጅመንት በአራተኛው ሩብ ዓመት የተካሄዱ የድጋፍና ክትትል ሥራዎች ሪፖርት ቀርቧል።
ከቀረቡት ሪፖርቶች በመነሳት የተለያዩ የሥራ አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖች በስፋት ተገምግመዋል። በተለይም በጥሩ ደረጃ የተከናወኑ ሥራዎችን ይበልጥ በማጠናከርና ወደፊትም በቀጣይነት እንዲተገበሩ ለማድረግ፣ እንዲሁም ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸውን የሥራ መስኮች በመለየት ተገቢውን የማሻሻያ እርምጃ ለመውሰድ በግምገማው መድረክ ላይ መግባባት ተደርሷል።
የግምገማው ዓላማ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር፣ የታዩ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን በመወሰን የጤና ኤክስቴንሽንና የቤተሰብ ጤና ቡድን አፈጻጸምን በቀጣይ ጊዜ የበለጠ ለማሻሻል ነው።
በመጨረሻም በግምገማው የተለዩ ጠንካራ አፈጻጸሞች እንዲጠናከሩ እና የማሻሻያ አቅጣጫ የተቀመጠላቸው የሥራ መስኮችም በቀጣይ የሥራ ዘመን በተጠናከረ ክትትል እንዲሻሻሉ ተስማምተዋል።

የነፍሰጡር እናቶች ፎረም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተካሄደ።************************ዛሬ በቀን 20/12/18 ዓም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአንደኛ ሩብ አ...
26/08/2026

የነፍሰጡር እናቶች ፎረም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተካሄደ።
************************
ዛሬ በቀን 20/12/18 ዓም በአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የአንደኛ ሩብ አመት የነፍሰጡር እናቶች ፎረም ተከናውኗል።
በእለቱም ሁሉም እናቶች ጤናማ የእርግዝና፤ የወሊድና የድህረ-ወሊድ ጊዜ እንዲያሳልፉ አስፈላጊውን የጤና መረጃ እንዲኖራቸው የሚያግዝ የጤና ትምህርት ተሰጥቷል።
በርካታ ነፍሰጡር እናቶች በተሳተፉበት ፎረም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊ እናቶችም ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረኩ መልስ ተሰጥቶባቸዋል።

አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እያከውናቸው ከሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች አካል የሆነ ‘በጎ አድራጎት ለጤናማ ማህበረሰብ’ በሚል መሪ ቃል በቀን 14/12/18 ዓ.ም የደም ግፊ...
21/08/2026

አላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እያከውናቸው ከሚገኙ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች አካል የሆነ ‘በጎ አድራጎት ለጤናማ ማህበረሰብ’ በሚል መሪ ቃል በቀን 14/12/18 ዓ.ም የደም ግፊት፤ የስኳር የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር፤ የHIV AIDS፤ የቲቢ ፣የአይን ምርመራ ዘመቻ እንዲሁም በርኆቦት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት የህክምና ድጋፍ አከናውኗል።
በሆስፒታሉ የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት ሀኪም በተመራው በጎ አድራጎት፣ የዕድገት ክትትል፣ ስር የሰደደ ሕመም፣የአጥንት ችግር ፣ በአይረን እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ፣አካል ጉዳተኝነት እንዲሁም ከውልደት የመጣ የአፈጣጠር ችግር የምርመራና የህክምና አገልግሎት በበጎ አድራጐት ተቋሙ ተጠልለው ላሉ ህፃናት ተደርጐላቸዋል።
እንዲሁም በታቦር ክፍለከተማ ፋራ ቀበሌ አዲሱ መናሀሪያ አካባቢ በተካሄደው ዘመቻ በርካታ የማህበረሰብ ከፍል አገልግሎት ያገኘ ሲሆን መርሀግብሩም በተለያዩ አዝናኝ ዝግጅቶች ታጅቦ ውሏል።

‎የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የአራተኛ ሩብ አመት ስብሰባና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የአቅመደካማ ቤት እድሳት የማስጀመር መርሀግብር አካሄደ።**...
19/08/2026

‎የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የአራተኛ ሩብ አመት ስብሰባና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የአቅመደካማ ቤት እድሳት የማስጀመር መርሀግብር አካሄደ።
********************************
‎የአላሙራ የመጀመሪያ ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ የ2018 ዓም የአራተኛ ሩብ አመት ስብሰባውን ና በሆስፒታሉ የሚከናወነውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነ የአቅመደካማ ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሀግብር አከናውኗል።
‎የሆስፒታሉን የቦርድ ስብሰባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ፣ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ እና የሆስፒታሉ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አገና ነቶ መርተውታል።
‎በመድረኩ የ2018 ዓም አፈፃፀም፣ የ2019 እቅድ፣ በባለፈው ስብሰባ በቦርዱ ውሳኔ ተላልፎባቸው የነበሩ ተግባራትን የአፈፃፀም ደረጃ እና በቀጣይ ውሳኔ የሚፈልጉ ጉዳዮች ሪፖርት በሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዮሴፍ ዮዌ ቀርቧል።
ስራ አመራር ቦርዱም በተቋሙ የጤና አገልግሎት ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶች፣ የታዩ ችግሮችና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራት ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዷል።
ልዩ ትኩረት የሚሹ እና ውሳኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮችን የገመገመው ቦርዱ፣ አገልግሎቱን ማዘመን (ዲጂታላይዜሽን)፣ የተቋሙ የG+3 ህንፃ ስራን ማስጨረስ፣ የባለሞያ የስራ ቅጥር ፍላጎትን ማሟላትና የትራንስፎርመር ግዢ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል ናቸውም ብሏል።
የተቋሙ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አጋና ኔቶ ሆስፒታሉ በዓመቱ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች አድንቀው፣ የተገኙ ስኬቶችን ማስቀጠልና ጉድለቶችን በአጠረ ጊዜ ለመፍታት በቅንጅትና በላቀ ቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።

11/08/2026
የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማናጅመንትና ሰራተኞች ከክፍለተማና ከቀበሌ አመራሮች ጋር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርና ፅዱ፣ ውብና ምቹ የስራ ከባቢን የመፍጠር ኢኒሼቲቭ አካል...
01/08/2026

የአላሙራ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማናጅመንትና ሰራተኞች ከክፍለተማና ከቀበሌ አመራሮች ጋር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባርና ፅዱ፣ ውብና ምቹ የስራ ከባቢን የመፍጠር ኢኒሼቲቭ አካል የሆነውን የፅዳት ዘመቻ በቀን 25/11/18 ዓ.ም በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ እንዲሁም በሆስፒታሉ ዙሪያ ባሉ መንደሮች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከጠዋት 12:00 ጀምሮ በጋራ አካሂደዋል።

Address

Awassa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Alamura Primary Hospital , Hawassa posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share